Writing

በሴሬብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy) ሳቢያ የሚከሰት የጡንቻ መወጠር (Spasticity ) ሕክምና አማራጮች

Types of spasticity
 

በሴሬብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy) ሳቢያ የሚከሰት የጡንቻ መወጠር (Spasticity) ሕክምና አማራጮች

ሴሬብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy - CP) በማደግ ላይ ባለው ሕፃን አንጎል ላይ በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜ ወይም በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በሚደርስ ጉዳት ምክንያት የሚከሰት፣ የጡንቻን እንቅስቃሴ፣ ሚዛን እና አቀማመጥ የሚረብሽ የዕድሜ ልክ የጤና ሁኔታ ነው። ይህ ሁኔታ Motor  (የእንቅስቃሴ) ችግሮችን ብቻ ሳይሆን የአእምሮና የመማር እክሎች፣ የንግግር እና የመዋጥ ችግሮች፣ የሚጥል በሽታ፣ እንዲሁም የእይታና የመስማት ችግሮችን የመሳሰሉ ተያያዥ አካላትን ሊይዝ የሚችል ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩት ዋና ዋና ችግሮች አንዱ የጡንቻ መወጠር (Spasticity ) በመባል ይታወቃል። 
 

1. Therapies

ለጡንቻ መወጠር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ሕክምና  ሲሆን የጡንቻን ልስላሴና ተንቀሳቃሽነት ለመጠበቅ ይረዳል።
  • Physical Therapy : የጡንቻን መወጠር ለመቀነስ፣ የመገጣጠሚያዎችን እንቅስቃሴ (Range of motion) ለማስፋት እና ሚዛንን ለመጠበቅ የሚረዱ እንቅስቃሴዎች ይሰጣሉ።
  • Occupational Therapy : ታካሚዎች ዕለታዊ የኑሮ ክህሎቶችን (እንደ መብላት፣ መልበስ እና ራስን መንከባከብ ያሉ) በራሳቸው እንዲሠሩ ለማስቻል ይረዳል።
  • Orthotics & Assistive Devices: እንደ እግር ማሰሪያዎች (Braces/Splints)፣ መራመጃዎች እና ዊልቸር ያሉ መሣሪያዎች የአካል ቅርጽ መዛባትን ለመከላከል እና እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ ያገለግላሉ።

2. የመድኃኒት ሕክምናዎች (Medications)
 ለከፋ የጡንቻ መወጠር የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ፣ በጡንቻዎች ላይ የሚኖረውን ከመጠን ያለፈ ግፊት ይቀንሳሉ።
  • በአፍ የሚወሰዱ መድኃኒቶች: እንደ Baclofen,Tizanidine, Diazepam  ያሉ መድኃኒቶች ማዕከላዊውን የነርቭ ሥርዓት በማስታገስ የጡንቻ መኮማተርን ይቀንሳሉ።
  • የቦቶክስ (Botulinum Toxin) መርፌ: ለአካባቢያዊ የጡንቻ መወጠር በጣም ውጤታማ ነው።  (ከ3 እስከ 6 ወራት የሚቆይ ውጤት ይኖረዋል)።
  • የባክሎፌን ፓምፕ (Intrathecal Baclofen Pump): ከባድ ስፓስቲሲቲ ላላቸው ታካሚዎች በቀዶ ሕክምና ከቆዳ ስር የሚቀበር መሣሪያ ሲሆን፣ መድኃኒቱን በቀጥታ ወደ አከርካሪ ፈሳሽ እንዲገባ በማድረግ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ይቀንሳል።
3. የቀዶ ሕክምና አማራጮች (Surgical Interventions)
ሌሎች ሕክምናዎች ውጤት በማይሰጡበት ጊዜ ወይም ከባድ የአካል ጉዳት መዛባት (Contractures) ሲከሰቱ የሚከተሉት የቀዶ ሕክምና አማራጮች ይታሰባሉ።
  • የጅማት ማራዘም ቀዶ ሕክምና (Tendon Lengthening):  ጅማቶችን በማራዘም የመንቀሳቀስ ነፃነትን ይሰጣል።
  • ሴሌክቲቭ ዶርሳል ራይዞቶሚ (Selective Dorsal Rhizotomy - SDR): የአከርካሪ ነርቭ ሥሮች ክፍልፋዮችን  በመቁረጥ ከመጠን ያለፈውን የነርቭ ንዝረት ቋሚ በሆነ መልኩ ማስተካከል ይቻላል።
  • ኒውሮቶሚ (Neurotomy / ፐርኩቴንየስ ራዲዮፍሪኩዌንሲ ኒውሮቶሚ): ለከፍተኛ እና ለአካባቢያዊ (Localized) የጡንቻ መወጠር የሚሰጥ የታለመ የቀዶ ሕክምና አማራጭ ነው።

 በዶ/ር ሱራፌል መኮንን 

 

 



Message on Telegram