Writing

Posterior reversible encephalopathy syndrome

T1 ,t2 DWI and ADC map images of PRES In 30 year old eclamptic patient
 

Posterior Reversible Encephalopathy Syndrome (PRES)
በአንጎል ደም ስሮች እና ህዋሳት (tissues) ውስጥ የሚከሰት የፈሳሽ መከማቸት (Vasogenic Edema) ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በአንጎል የኋላ ክፍል (Parieto-occipital region) ላይ ይከሰታል።
                                                   በ MRI የሚታዩት (MRI Findings)
ለአብነት ያህል ከላይ የቀረቡትን የ MRI ምስሎች ስንመለከት የ Posterior Reversible Encephalopathy Syndrome ባህሪያትን በግልፅ ያሳያሉ፡
                          T1 እና T2 Weighted Sequences (ምስል 1):

  • በ T1-weighted MRI ላይ በፓራየቶ-ኦክሲፒታል (Parieto-occipital) አካባቢዎች አነስተኛ የሲግናል ቅናሽ (Hypointensity) ይታያል።

  • በ T2-weighted MRI ላይ በሁለቱም በኩል ባሉ የፓራየቶ-ኦክሲፒታል ንዑስ-ኮርቲካል ነጭ አንጎል (Subcortical white matter) ክፍሎች ላይ ጎልቶ የሚታይ የሲግናል ጭማሪ (T2 Hyperintensity) ይታያል። ይህ የሚያሳየው የፈሳሽ መከማቸትን (Vasogenic Edema) ነው።
                                 DWI እና ADC Map (ምስል 2):

  • በ Diffusion-Weighted Imaging (DWI) እና በ Apparent Diffusion Coefficient (ADC) map ላይ የሚታየው ከፍተኛ የ ADC ሲግናል (T2 shine-through effect) በ አንጎል ውስጥ ያለው ፈሳሽ Vasogenic Edema እንጂ ህዋሳት በመሞታቸው የሚመጣ Cytotoxic Edema (Ischemic Stroke) አለመሆኑን ያረጋግጣል።
     
                         ዋና ዋና መንስኤዎች እና ተጋላጭነቶች

  • ከፍተኛ የደም ግፊት (Hypertensive Emergency): የደም ግፊት በድንገት እና በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የአንጎል ደም ስሮች የደም ፍሰቱን መቆጣጠር (Autoregulation) ያቅታቸዋል።

  • የእርግዝና  ደም ግፊት (Pre-eclampsia / Eclampsia): በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ በሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት ምክንያት የሚመጣ።

  • የኩላሊት ህመም (Renal Disease): የኩላሊት ድገተኛ ወይም የረጅም ጊዜ ስራ ማቆም ባላቸው ታካሚዎች ላይ ይከሰታል።

  • የካንሰር መድሃኒቶች (Immunosuppressants & Cytotoxic drugs): እንደ Cyclosporine, Tacrolimus ወይም የካንሰር ህክምና (Chemotherapy) የሚከታተሉ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል።

  • የሰውነት መከላከያ ስርዓት መዛባት (Autoimmune diseases): እንደ Lupus (SLE) እና ከባድ የኢንፌክሽን ሁኔታዎች (Sepsis)።

                    ዋና ዋና የህመም ምልክቶች

  • የአንቀጥቅጥ ህመም (Seizures): ከ 70% እስከ 80% በሚሆኑ ታካሚዎች ላይ የሚታይ በጣም የተለመደ ምልክት ነው።

  • የእይታ መዛባት (Visual Disturbances): የአንጎል የኋላ ክፍል (Occipital lobe) ስለሚጠቃ እይታ ማደብዘዝ፣ በፊታችን ላይ ጥላዎች ማየት ወይም ጊዜያዊ የዓይን ብርሃን ማጣት (Cortical blindness) ሊከሰት ይችላል።

  • የአስተሳሰብ እና ንቃተ-ህሊና መዛባት (Encephalopathy): ግራ መጋባት፣ ከባድ ድብታ ወይም እስከ ራስን መሳት የሚደርስ ደረጃ።
  • ኃይለኛ የራስ ምታት (Headache): በድንገት የሚመጣ እና ከባድ የሆነ የራስ ምታት።

                                   ህክምና እና የህመሙ ሂደት

  • ህመሙ በጊዜ ደርሶ ትክክለኛ ህክምና ከተሰጠ ሙሉ በሙሉ የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነው (Reversible)።
  • የደም ግፊትን መቆጣጠር: በነርቭ እና በፅኑ ህክምና ክፍሎች (ICU) የደም ግፊትን በጥንቃቄ እና በደረጃ መቀነስ።
  • መንስኤውን ማስወገድ: ህመሙን ያመጡ መድሃኒቶችን ማቆም ወይም መተካት፣ እንዲሁም በእርግዝና ወቅት ከሆነ ህፃኑን በፍጥነት ማገገዝ።
  • መድሃኒቶች: መንቀጥቀጥን የሚያቆሙ (Antiseizure medications) መስጠት።


 
Message on Telegram