የሕፃናት አንጎል እጢ እንዴት ይታከማል?
የሕፃናት አንጎል እጢ እንዴት ይታከማል?
የአንድ ሕፃን ጭንቅላት ውስጥ እጢ እንዳለ መስማት ለቤተሰብ እጅግ አስጨናቂ እና ከባድ ነው። ቀጣዩ እና ዋናው ጥያቄ "ታዲያ ይታከማል ወይ?" የሚለው ነው።
አዎ! ይታከማል። ነገር ግን የሕክምናውን ሂደት እና ዓላማ በደንብ መረዳት ያስፈልጋል። የህክምናው ዓላማ እንደ እጢው ሁኔታ እና እንደ እያንዳንዱ ሕፃን ሁኔታ ይለያያል።
የህክምና ሂደቱን እና ውጤቱን የሚወሰኑ ዋና ዋና ነጥቦች፦
፩. እጢው የበቀለበት የአንጎል ክፍል
እጢው የሚገኝበት ቦታ ለህክምናው ወሳኝ ነው። ለምሳሌ እንደ አተነፋፈስ እና የልብ ምትን የሚቆጣጠሩ በጣም አስፈላጊ የአንጎል ክፍሎች ላይ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ በቀዶ ጥገና ለማንሳት መሞከር አደገኛ ሊሆን ይችላል። በእንዲህ አይነት ወቅት አነስተኛ ናሙና (Biopsy) ብቻ ከተወሰደ በኋላ እንደ እጢዉ አይነት በኬሞቴራፒ (በመድኃኒት) ወይም በጨረር ይታከማል።
፪. እጢው በአቅራቢያው ባሉ ነርቮች ላይ የሚያደርሰው ጫና
እጢው በአንጎል ውስጥ ባሉ ዋና ዋና ነርቮች (Cranial nerves) ላይ የሚያሳድረው ጫና ህክምናውን አስቸኳይ ያደርገዋል። ለምሳሌ እጢው በዕይታ ነርቭ (Optic nerve) ላይ ጫና ካሳደረ የሕፃኑን እይታ ስለሚያሰጋ ቀዶ ጥገናው በአስቸኳይ መደረግ ሊኖርበት ይችላል።
፫. የአንጎል ውስጥ ውኃ መከማቸት (Hydrocephalus)
እጢው የአንጎል ውኃ ፍሰትን በመዝጋት የጭንቅላት ውጥረት በሚፈጥርበት ጊዜ፣ የውኃ መከማቸቱን (Hydrocephalus) ማከም ሁልጊዜም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው እና አጣዳፊ ተግባር ነው። ይህ ህክምና እጢውን ከማንሳታችን በፊት ወይም ከእጢ ቀዶ ጥገናው ጎን ለጎን ወዲያውኑ መከናወን ሊኖርበት ይችላል ።
፬. የእጢው ቆይታ እና የዕድገት ፍጥነት (Duration of the lesion)
እጢው በጭንቅላት ውስጥ የቆየበት ጊዜ እና የእድገት ፍጥነቱ በህክምና ውሳኔ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።
፭. የእጢው ደረጃ እና ሞለኪዩላር ዓይነት (Grade & Molecular subtype)
የአንጎል እጢዎች እንደ ባህሪያቸው ከደረጃ 1 እስከ 4 ይከፈላሉ፦
ደረጃ 1 እና 2 (ቀስ ብለው የሚያድጉ)፦ አብዛኛውን ጊዜ በቀዶ ጥገና ሙሉ በሙሉ በማንሳት ብቻ ሊድን ይቻላል።
ደረጃ 3 እና 4 (ፈጣን እድገት ያላቸው)፦ ቀዶ ጥገና ተደርጎ ከተነሳ በኋላ እጢው ተመልሶ እንዳያድግ ተጨማሪ የጨረር እና የኬሞቴራፒ ህክምና ያስፈልጋቸዋል።
፮. የእጢው መጠን እና ሙሉ በሙሉ የመነሳት እድል (Resectability)
እጢው በቀዶ ጥገና ሙሉ በሙሉ ሊነሳ የሚችልበት ደረጃ ላይ መሆኑ (Gross Total Resection) ወይም የተወሰነው ክፍል ብቻ የሚነሳ መሆኑ ለህክምናው ስኬት ትልቅ ድርሻ አለው።
፯. የሕፃኑ ዕድሜ እና አጠቃላይ የጤና ሁኔታ
ከ 3 ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት የአንጎል እድገታቸውን ለመጠበቅ ሲባል የጨረር ህክምና አይሰጥም። ይልቁንም ቀዶ ጥገና እና የኬሞቴራፒ ህክምና ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
ቤተሰቦች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ጥያቄ፦ "የህክምናው ውጤት ወይም የማገገም እድሉ (Prognosis) ምን ያህል ነው?"
የሕፃናት አንጎል እጢ ህክምና ውጤት (Prognosis) ለእያንዳንዱ ሕፃን የተለየ (Individualized) ነው።
አንድ ሕፃን የማገገም እድሉ ምን ያህል እንደሆነ የሚወሰነው ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች : ማለትም የእጢው ቦታ፣ ደረጃው፣ ሙሉ በሙሉ መነሳት መቻሉ፣ የሕፃኑ ዕድሜ፣ እና የህክምናው የጊዜ አጣዳፊነት—በአንድ ላይ ተደምረው በሚሰጡት ውጤት ነው። ስለዚህ ለአንዱ ሕፃን የሚሰጠው ህክምና ለሌላው ሕፃን ሙሉ በሙሉ የተለየ ሊሆን ይችላል።
በሚቀጥለው ክፍላችን፦
ስለ ህፃናት አንጎል እጢዎች የተለያዩ ምልክቶች በስፋት የምንወያይ ይሆናል