Craniosynostosis ምንድን ነው?
ስለ Craniosynostosis እና የቀዶ ህክምናው ማወቅ የሚገቡዎት ነጥቦች
የህፃናት የራስ ቅል እድገት ለአእምሮ መስፋፋትና ለጭንቅላት ቅርፅ ምቹ እንዲሆን በተለያዩ አጥንቶች ተከፋፍሎ የተሰራ ነው። እነዚህ አጥንቶች እርስ በርሳቸው የሚያያዙበት መስመር Cranial Suture ይባላል። Craniosynostosis የሚከሰተው ህፃናት ሲወለዱ ወይም በተወለዱ በወራት ጊዜ ውስጥ እነዚህ የራስ ቅል የመገጣጠሚያ መስመሮች ያለጊዜያቸው ቀድመው ተጣብቀው ሲዘጉ ነው። ቀድመው መዘጋታቸው የራስ ቅል ቅርፅ እንዲቀየር ያደርጋል፤ እንዲሁም እያደገ የሚሄደው የአእምሮ ክፍል በቂ ቦታ እንዳያገኝ በማድረግ የጭንቅላት ውስጥ ጫና (Increased Intracranial Pressure) ሊፈጥር ይችላል።
ብዙ ወላጆች የህፃናት የራስ ቅል ቅርፅ መዛባትን እንደ ተፈጥሮአዊ ልዩነት በመቁጠር ህክምና ፍለጋ የሚመጡት ዘግይተው ነው። ነገር ግን ስለ Craniosynostosis ህብረተሰቡ ያለው ግንዛቤ ማደጉ ህፃናት ገና በጨቅላነታቸው በስፔሻሊስት ታይተው በወቅቱ ህክምና እንዲያገኙ እና ሊከሰቱ የሚችሉ የአእምሮ እድገትና የእይታ ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
የCraniosynostosis አይነቶች እና Positional Plagiocephaly
የተዘጋው የመገጣጠሚያ መስመር አይነት እንደ ሁኔታው የተለያዩ የራስ ቅል ቅርፅ መዛባቶችን ያስከትላል፡
Sagittal Synostosis (Scaphocephaly): የጭንቅላት የላይኛው መስመር ሲዘጋ የሚከሰት ሲሆን፣ የራስ ቅሉ ወደ ጎን ቀጭን ሆኖ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ይረዝማል።
Coronal Synostosis: የፊት ለፊት ጎን መስመር ሲዘጋ የሚከሰት ሲሆን፣ ግንባር እና የአይን አካባቢ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ያደርጋል።
Metopic Synostosis (Trigonocephaly): የግንባር ማዕከላዊ መስመር ሲዘጋ የሚከሰትና ግንባር ሶስት ማዕዘን ቅርፅ እንዲይዝ የሚያደርግ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የራስ ቅል ቅርፅ መዛባት Positional Plagiocephaly (በአንድ ቦታ ብቻ በመተኛት የሚመጣ የራስ ቅል መጣመም) ሊከሰት ይችላል። ይህ ሁኔታ የአጥንት መገጣጠሚያ መስመሮች በመዘጋታቸው የሚመጣ ሳይሆን ህፃኑ በተደጋጋሚ በአንድ በኩል ብቻ ተኝቶ በሚፈጠር ጫና የሚከሰት ነው።
Positional Plagiocephaly እንዴት ይስተካከላል?
1. Tummy Time (በሆድ ማስተኛት): ህፃኑ ነቅቶ በሚቆይበት ጊዜ በሆዱ እንዲተኛ በማድረግ በጭንቅላቱ ኋላ ላይ የሚወርደውን ጫና መቀነስ።
2. የአቀማመጥ ቅያሬ (Repositioning): በሚተኙበት ወቅት የጭንቅላታቸውን አቅጣጫ በየጊዜው መለወጥ።
3. Cranial Helmet Molding Therapy: በከባድ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሁኔታዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ የራስ ቅል ማስተካከያ ቆብ (Helmet) መጠቀም።
የቀዶ ህክምና (Surgical Management) አማራጮች
የCraniosynostosis ቀዶ ህክምና ዋና አላማ በጭንቅላት ውስጥ ለአእምሮ እድገት የሚሆን በቂ ቦታ መፍጠር እና የራስ ቅል ቅርፅን ማስተካከል ነው። ህክምናው እንደ ህፃኑ እድሜ እና እንደ ሁኔታው በተለያዩ መንገዶች ይሰጣል፡
Endoscopic Strip Craniectomy :
ይህ ህክምና እድሜያቸው ከ3 እስከ 6 ወር ላሉ ህፃናት የሚደረግ ሲሆን፣ በትንሽ ቀዳዳ በኩል በካሜራ (Endoscope) ታግዞ የተዘጋውን አጥንት መስመር የማላቀቅ ስራ ይሰራል። ከህክምናው በኋላ በባለሙያዎች የተሰራ Cranial Helmet Molding Therapy ጥቅም ላይ ይውላል።
Open Cranial Vault Remodeling :
እድሜያቸው ከ6 ወር በላይ ለሆኑ ህፃናት ወይም ከብዙ የመገጣጠሚያ መስመሮች መዘጋት ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ሁኔታ የሚደረግ ሲሆን፣ የራስ ቅል አጥንትን በማስተካከልና ቅርፅ በመስጠት አእምሮው በቂ ቦታ እንዲያገኝ ይደረጋል።
ይህ የCraniosynostosis የነርቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የነርቭ ቀዶ ህክምና ክፍል (St. Paul's Hospital Department of Neurosurgery) በህፃናት ነርቭ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት (Pediatric Neurosurgery Specialist) እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ስለ ሁኔታውና ህክምናው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት drsurafel.com መጎብኘት ይችላሉ።